loader
የቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2011 ዓ. ም. የዓለም ዜና

የቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2011 ዓ. ም. የዓለም ዜና

በኢትዮጵያ በቅርቡ የተካሄዱት የጅምላ እስሮች እና "አመለካከትን የመቀየር ስልጠናዎች" ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሯቸውን ፖለቲካዊ ማሻሻያዎች አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሃድሶ ስልጠና የሚሰጥባቸውን ካምፖች እንዲዘጉ እና የዘፈቀደ እስርንም በማስቆም ቁርጠኝነታቸውን እንዲያሳዩም አሳስቧል። 

- “ወጣቶችን አስተባብራችሁ አመጽ ልታነሳሱ ነበር” በሚል ተጠርጥረው ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በእስር ላይ የቆዩት ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ እና ማይክ መላክ ዛሬ ከእስር ተለቀቁ። ግለሰቦቹ የተለቀቁት ለራሳቸው ዋስ እንዲሆኑ ተደርጎ ነው መሆኑን ጠበቃቸው ገልጸዋል። 

- በታንዛንያ መዲና ዳሬሰላም ከሳምንት በፊት ታግቶ የነበረው ታንዛኒያዊ ቱጃር ዛሬ መለቀቁን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ። ታንዛኒያዊው ቢሊየነር ሞሃመድ ዴውጂ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስበት ወደቤቱ ተመልሷል ተብሏል።  

- በስፔን ማድሪድ በማቆያ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ ስደተኞች ለማምለጥ ባደረጉት ሙከራ 10 ፖሊሶች እና አንድ ስደተኛ ላይ ጉዳት መድረሱን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ። ስደተኞቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተወሰነባቸው ነበሩ። 

- በአፍጋኒስታን ከዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ጋር በተያያዘ በተከሰተ ብጥብጥ 170 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ። በካቡል በሚገኝ የድምጽ መስጫ ጣቢያ ዛሬ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ 15 ሰዎች ሲገደሉ 20 ቆስለዋል።

???? የዕለቱን ዜና ለማድመጥ ይህንን ማገናኛ (ሊንክ) ይጫኑ ???? https://www.wbca.st/zjrF7Cw

Rachid Nekkaz will do anything to be

In 2007, Rachid Nekkaz’s bid to become president of France failed as he fell short of the 500 endorsements from people holding political office, required to contest.

In 2019, Rachid Nekkaz’s bid to become president of Algeria, failed even though he raised the 60,000 voter signatures required to

የአዲስ አበባ ፖሊስ

 ፖሊስ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ተላልፎ ሰልፍ የሚወጣ ካለ እርምጃ ይወሰዳል ብሏል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነገው ዕለት በከተማዋ እምብርት መስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ እንዳልቀረበ

የእሁድ የካቲት 10 ቀን

በአማራ ክልል ከጎንደር እስከ መተማ በተዘረጋው አውራ ጎዳና ሰዎች እንደሚታፈኑ እና መኪናዎችም በጥይት እንደሚመቱ አንድ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ። በዚህ መንገድ በአምስት ኪሎ ሜትር ክልል በግልም

ኢትዮጵያዊው ሳሙኤል


ባለፈው ሳምንት ክብረ-ወሰኑን ለማሻሻል 0.01 ሰከንድ ብቻ ሲቀረው ውድድሩን ያጠናቀቀው ሌላው ኢትዮጵያዊ ዮሚፍ ቀጀልቻ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ዮሚፍ በዚህ ውድድር የዓለም ክብረ-ወሰንን የማሻሻል ዕቅድ

ወደ ደቡብ አፍሪቃ

ይሁን እና እስካሁን ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት እየጠበቀ እንደነበር ገልጿል። ሟቾቹ በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን ኤምባሲው ጠቁሟል። አስከሬኑ ወደ ኢትዮጵያ ያልተላከበትን ምክንያት ኤምባሲዉ አልገለፀም።

(ፎቶ

አረና የወሰን እና

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው አረና ተቃውሞውን እና ጥያቄውን ያሰማው የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ በመቀሌ ከተማ ካካሄደው መደበኛ ስብሰባ በኋላ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ፓርቲው በፌደራል መንግስት

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ

ባለፈው ሰኔ የተቋቋመው ይህ ኮሚቴ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ካጠናቸው ሶስት ጉዳዮች አንዱ የመጅሊስ መዋቅር እና ምርጫ ጉዳይ መሆኑን በዛሬው መግለጫው አስታውቋል። የኮሚቴው ሰብሳቢ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ

የረቡዕ የካቲት 6 ቀን 2011

- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ያልጀመሩ እና መሠረት ብቻ አውጥተው ወደ ግንባታ ያልገቡ የሪልስቴት ኩባንያዎችን ቦታን ለመንጠቅ ወሰነ። አስተዳደሩ «ተመላሽ አደርጋለሁ» የሚለዉ ቦታ ለከተማይቱ

ኢትዮጵያ ለዓለም ንግድ

ለአፍሪቃ ኅብረት ስብሰባ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙት ዋና ዳይሬክተሩ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው በሒደቱ ላይ መወያየታቸውን በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ አስታውቀዋል። ከሮቤርቶ

በአዲስ አበባ ከተማ

አጣሪ ኮሚቴው በጉዳዩ ላይ ያጠናቀረውን ጥናት በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት አቅርቧል። በጥናቱ መሠረት ከ120 ኩባንያዎች 19 በአግባቡ ሥራቸውን በማከናወን ላይ