loader
የኅዳር 2 ቀን 2011 ዓ.ም የዓለም ዜና

የኅዳር 2 ቀን 2011 ዓ.ም የዓለም ዜና

በደብረማርቆስ እና ፍኖተሰላም ከተሞች በዛሬው እለት ሠላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ። በዋናነት ወጣቶች ተካፋይ በኾኑበት ሰልፎች ፍኖተሰላምላይ የየከተማዎቹ ነዋሪዎች እና የመንግሥት ባለሥልጣናትም መሳተፋቸው ተገልጧል። የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ አንማው ዳኛቸው ለDW እንደገለፁት በሰልፎቹ ላይ አራት ዐበይት ነጥቦች ተንጸባርቀዋል።  

«አንደኛ የወልቃይት እና የራያ ማንነት ጥያቄዎች በአፋጣኝ  መመለስ ይገባቸዋል የሚል ነው፤ ኹለተኛ የዜጎች መገደል እና መፈናቀል ይቁም በሚል ነው፤ ሦስተኛ የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት የአማራነት መለያ ነውና  በአስቸኳይ ይታደስ እና ወደነበረበት ይመለስ የሚል ነው፤ አራተኛው ደግሞ ጣና ታሟልና  ልንደርስለት ይገባል በሚል ጣናንም የያዘ ነው።»

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከብር ሸለቆ የእርሻ ልማት ጋር በተያያዘም ጥያቄ መነሳቱን አቶ አንማው ተናግረዋል። ተመሳሳይ ዓላማ ያነገበ እንደኾነ የተነገረለት ሌላ ሰልፍ በደብረማርቆስ ከተማ መከናወኑን በምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ  አቶ ጋሻዬ ጌታሁን ለDW ገልጠዋል።
 
«ሰልፉ በሠላም ነው የተጠናቀቀው።  በሰላም እንዲጠናቀቅ የደብረማርቆስ ወጣቶች ራሳቸውን የቻሉ መለያ ለብሰው  በሥነ ሥርዓት ያለምንም ኹከት እና ግርግር፤ ምንም አይነት ነገር ሳይፈጠር በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ያደረጉት አስተዋጽዖ ጉልኅ ነበር፤ ኅብረተሰቡ  ጥያቄውን ለማስተጋባት ነው እንጂ ሌላ ተልእኮም የነበረው አልነበረም። ስለዚህ በሠላማዊ መንገድ ነው የተጠናቀቀው።»

*በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በኢቦላ ተሐዋሲ የተነሳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 200 መድረሱ ተዘገበ።  በመዲናዪቱ ኪንሻሳ የሚገኘው የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚንሥቴር ከነሐሴ ወር ጀምሮ 291 ሰዎች የኢቦላ ተሐዋሲው እንደተገኘባቸው ዐስታውቋል። ግማሽ ያኽሉ ሰዎች የተመዘገቡትም ሠላም በራቀው የሰሜን ኪቩ አውራጃ ቤኒ ከተባለችው ከተማ ነው ብሏል። እንደ ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት (WHO) ከኾነ በአካባቢው ባለው ግጭት የተነሳ የክትባት ዘመቻዎች በተደጋጋሚ መሰናከል ይገጥማቸዋል። በአኹኑ ወቅት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ተሐዋሲ ካለፉት 40 ዓመታት ከነበረው እጅግ የከፋው ነው ተብሎለታል። 

*በጣሊያን መዲና ሮም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጥብቅ የስደተኞች ሕግን በመቃወም ዛሬ አደባባይ ወጡ። እንደ ሰልፉ አዘጋጆች ከኾነ ከሀገሪቱ 50 ከተሞች የተውጣጡ ሰዎች በሰልፉ ላይ ታድመዋል። የጣሊያን ምክር ቤት ስደተኞችን በቀላሉ ወደ መጡበት ለመመለስ እና የአንዳንዶቹን ስደተኞች የጣሊያን የመኖሪያ ፍቃድ መሰረዝ የሚያስችለውን አዋጅ ያሳለፈው ከጥቂት ቀናት በፊት ነው። ሕጉ በጣሊያን ቀኝ ዘመም የሀገር ውስጥ ሚንሥትር ማቴዎ ሣልቫኒ ገፋፊነት ነበር ለምክር ቤት የቀረበው። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR) በጣሊያን ምክር ቤት አዋጅ ስጋት እንደገባው ገልጧል። 

*በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ማብቂያን ለማሰብ  ወደ 70 የሚጠጉ ርእሰ-ብሔራት እና ባለሥልጣናት በዛሬው እለት ተሳተፉ። በመታሰቢያው ላይ የተገኙት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑዌል ማክሮ፦ ዓለም ከጽንፍ ብሔርተኝነት እና ስግብግብነት ሊጠበቅ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል። በመታሰቢያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከታደሙ የዓለም መሪዎች መካከል የጀርመን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል፤ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ  እና የሩስያው ፕሬዚዳንት ብላድሚር ፑቲን  ይገኙበታል። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ1918 በዛሬው እለት የጥምር ኃይላቱ የፈረንሳይ እና የብሪታንያ ጦር ከጀርመን ጦር ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ያደረጉበት ቀን ሲኾን፤ እለቱ የጀርመን ጦር እጅ የሰጠበትም ነው። 

*በካሊፎርኒያ ግዛት በተቀሰቀሰው የጫካ ሰደድ እሳት የተነሳ ቢያንስ 25 ሰዎችን ሞቱ። በሰሜን ካሊፎርኒያ ብቻ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 23 መድረሱን የአካባቢው የእሳት አደጋ መከላከያ ጠቅሷል።  በእሳት ጋይተው አመድ ከኾኑት ቤቶች ምናልባትም ሌሎች ተጨማሪ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተሰግቷል። ማሊቡ በተባለችው የባሕር ዳርቻ ከተማ ኹለት ሰዎች መሞታቸው ተገልጧል። በፓራዲዝ ብቻ 6450 በመኖሪያ ቤቶች በእሳት ጋይተዋል። በብርቱ ንፋስ የተነሳ እሳቱ ሊያይል እና ተጨማሪ አደጋ ሊፈጥር እንደሚችል ባለሞያዎች ከወዲሁ አስጠንቅቀዋል።
 
https://www.wbca.st/5WnShyw

ሳዑዲ አረቢያ

ቱርካዊት እጮኛውን ሊያገባ የቆረጠው ጀማል ኻሾግጂ ከመንግሥቱ የሚያስፈልገውን ሰነድ ፍለጋ መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ.ም. በቱርኳ የኢስታንቡል ከተማ በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ቆንስላ ገብቶ አልተመለሰም።  ኻሾግጂ

ቻይና በቅርቡ ሁለተኛ

ቻይና ልትሠራው ነው የተባለው ሰው ሠራሽ ጨረቃ ሠረቀ-ብርሃን ከተፈጥሮዋ ጨረቃ በስምት እጥፍ ይልቃል ተብሏል። ሰው ሠራሿ ጨረቃ ከሁለት ዓመት በኋላ በሲቹን አውራጃ መዲና ቼንግዱ ሠማይ ላይ ተዘርግታ ብርሃን

 U.S. Deputy Chief of Mission in

U.S. Deputy Chief of Mission in Ethiopia, Troy Fitrell, said Ethiopians need to cooperate with the new Ethiopian government so that the reform underway can attain its goals, according to ENA report.

In an exclusive

2 children killed in Tripoli as

Two children were killed after a missile struck a house in Tripoli, Libya on Thursday during ongoing clashes between rival Libyan factions.

According to the local municipal council, the children aged 6 and 14 were reportedly playing in a garden when the missile hit their home.

Egypt, Sudan to negotiate on El-Nakda

This meeting was held on the back of the ministerial committee meeting.

“I see a positive attitude on the part of the (Ethiopian) Prime Minister to eliminate all obstacles, as well as a concern to assign new representatives to remain in constant and intensive communication (with

Outrage in Morocco as 17-year old girl

A Moroccan teenager has aroused emotions and sparked outrage after alleging kidnap, rape and torture by some fifteen individuals for two months in Oulad Ayyad, in the administrative region of Morroco.

“They sequestrated me for almost two months, raped and tortured, I will never

South Africa bus crash leaves at least

The accident occurred at around 2 a.m. (2400 GMT) 50 kilometres outside Beaufort West, a town in the semidesert Karoo region. Another 30 passengers were injured.

“The driver apparently lost control of the vehicle which then overturned,” said Kenny Africa, provincial traffic

Zimbabwe 2018 vote: Mugabe,

Mugabe, the revolutionary leader turned Prime Minister and President, had led the country for over three decades but was deposed in a November 2017 military takeover – he insists was a coup.

In a country where campaigning ceases 24-hours to the polls, Mugabe, however, managed to

US Delegation Visits Ethiopia to

A U.S. delegation is heading to Ethiopia on Wednesday to talk about the country’s reform efforts since Prime Minister Abiy Ahmed took office in April.

Republican Congressman Christopher Smith, who led the

የደቡብ ሱዳን

በዛሬው ዕለት የተደረገው የሰላም ስምምነት በደቡብ ሱዳን ጦርነት ለመጨረሻ ጊዜ የሚያቆም መሆን እንዳለበት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ገልጸዋል፡፡

የዛሬው የሰላም ስምምነት ደቡብ ሱዳናውያን ብቻ

Top Headlines

Ethiopia

Top News

International

Top News