loader
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፍተኛ ከጦር አዛዦች እና ወታደራዊ አመራሮች ጋር ዛሬ ጠዋት በጽህፈት ቤታቸዉ ውይይት አድርገዋል። የዉይይቱ ዋና አላማም ከለዉጡ ወዲህ የመከላከያ ሰራዊቱን ዘመናዊ፣ ብቁና ዉጤታማ ለማድረግ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ታስቦ እንደሆነም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ዛሬ ባወጣዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፍተኛ ከጦር አዛዦች እና ወታደራዊ አመራሮች ጋር ዛሬ ጠዋት በጽህፈት ቤታቸዉ ውይይት አድርገዋል። የዉይይቱ ዋና አላማም ከለዉጡ ወዲህ የመከላከያ ሰራዊቱን ዘመናዊ፣ ብቁና ዉጤታማ ለማድረግ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ታስቦ እንደሆነም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ዛሬ ባወጣዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።

ለዚህ ዉይይትም «በቅርቡ በዉስን ወታደሮች የተከሰተዉን ከወታደራዊ ዲሲፕሊን ያፈነገጠ ድርጊት እንደ መነሻ መወሰዱ» በመግለጫዉ ተጠቅሷል። ባለፈው መስከረም 30 ወደ  240 የሚጠጉ ወታደሮች «የደሞዝ ጭማሪ» ጥያቄያቸዉን ለጠቅላይ ምኒስትር አብይ ለማድረስ ከእነትጥቃቸው ወደ ቤተመንግሥት ማቅናታቸዉ ድንጋጤ ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወታደሮች ጋር የተወያዩ ቢሆንም በስተኋላ ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ ድርጊቱን ኮንነዋል።  
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በዛሬው ውይይታቸው «መከላከያ ሰራዊት በአንድ አገር የሚኖር ብቸኛዉ የታጠቀ አካል በመሆኑ ይህን ኃላፊነት በሕገ መንግስታዊ መልኩ መወጣቱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን» ገልፀዋል። ሰራዊቱም «በህገ መንግስቱ በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት ለግዳጅ ሲሰማራ በታጠቀዉ መሳሪያ ምክንያት ኃይል ቢኖረዉም እርምጃዉ ቅብልነትን በሚያረጋግጥ መልኩ በከፍተኛ ጥንቃቄ፣ የሕግ ተገዥነትና የሕዝብ ተቆርቋሪነት ስሜት መከናወን እንዳለበት» ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል። «መከላከያ ሰራዊት ኃይል አለኝ ብሎ እርምጃ የማይወስድ ቢሆንም ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅ ግን በተሰጠዉ ስልጣን ልክ በጥብቅ የግዳጅ አፈፃጸም ተግባራዊ መፍትሄ መስጠት አስፈላጊ» ነዉ ብለዋል።
ፎቶ፥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

የዓለም ዜና ፤ ኅዳር 4፤

ቁጥጥር ስር የዋሉት የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እጃቸዉ በካቴና ታስሮ ከተያዙበት ቦታ በሄሌኮፕተር ወደ አዲስ አበባ ተወሰዱ። ሜጄር ጀነራል ክንፈ በ 48 ሰዓታት ዉስጥ ፍርድ ቤት

የቀድሞ የብሄራዊ

በአዲስ አበባ ብቻ ከሰባት በላይ ስዉር እስር ቤቶች እንደሚገኙም በምሳሌኔት ጠቅሰዋል። ተጠርጣሪዎቹን ብዙ ግዜ በአምቡላንስ እንደሚያጓጉዟቸዉ ከተያዙ በኋላ አይናቸዉን በመሸፈን ለረዥም ጊዜ እንዲቆዩ

በሞጆ የደረቅ ወደብ

በገቢዎች ሚኒስትር የኮሙዩኒኬሼን ጉዳይ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም መኮንን ለDW እንደተናገሩት የምግብ ዘይቱን ያስመጡት ነጋዴዎች የዕቃ ማጠራቀሚያ ኮንቴይነሮችን በቀጣይ ቀናት ካላነሱ ተወርሶ ለሽያጭ በጨረታ መልክ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት

የፕሬዚዳንቱ የጎንደር ከተማ ጉብኝት ለአንድ ቀን እንደሚቆይ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጠቅሷል። የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ ተጠቃሚዎች የኤርትራው ፕሬዝዳንት በአጭር ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ተደጋጋሚ ጉብኝት ለምን

እጅግ በፍጥነት

የአማራ ክልል የአካባቢ የደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለሥልጣንን ጠቅሶ የአማራ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገበው፦ አርሶ አደሮች ዛሬ እምቦጭ አረምን ሲያርሙ ውለዋል። ከ5,300 ሄክታር የሚበልጥ የጣና ሐይቅን

በደቡብ ክልል፤

በከምባታ ጠምባሮ ዞን የወረዳ ጥያቄ ያነሳችው አዲሎ የተባለችው ቀበሌ ውስጥ ትናንት፣ ጠምባሮ በተባለችው ወረዳ ላይ ደግሞ ከትናንት በስትያ ሰልፍ ነበር ብለዋል። ጠምባሮ ከተማ ራሱን ችሎ ጠምባሮ ከተማ አስተዳደር

ጡት እና የማሕጸን

ጡት እና የማሕጸን ካንሰር
ሴቶችን ከሚያጠቁ የካንሰር ዓይነቶች የጡት ካንሰር ግንባር ቀደም መሆኑ ይነገራል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው በመላው ዓለም በየዓመቱ ሁለት ሚሊየን ገደማ ሴቶች በጡት ካንሰር

ኢትዮጵያን ጨምሮ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በፕሬዚዳንቱ የአራት ዓመት የሥልጣን ዘመን አጋማሽ፥ በተለምዶ በየአራት ዓመቱ ጥቅምት ወር ላይ በሚካሄደው ምርጫ (mid-term elections) ሶማሊያዊቷ ኢልሀን ዖማር አሸንፋለች። ከ36 ዓመቷ የሚኒሶታ

የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ

የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኦዴፓ/ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆኖ መሾማቸዉን ዘገባዎች አመለከቱ። አዲሱ ተሿሚ የጠቅላይ

በአማራ ክልል እስካሁን

የክልሉ ምክር ቤት በትናንትና ውሎው የክልሉን የትምህርት ዘርፍ ዓመታዊ አፈፃፀም ገምግሟል፡። የምክር ቤት አባላት እንደጠቆሙት በክልሉ ለትምህርቱ ዘርፍ ተገቢው ትኩረት ባለመሰጠቱ በትምህርት ጥራት ላይ ተጽዕኖ

Top Headlines

Ethiopia

Top News

International

Top News