[1:12 PM, 10/29/2018] የዶይቸ ቬለ ዜና: በምዕራባዊ ኦሮሚያ ክልል በሚገኙት አከባቢዎች የኦሮሞ ነፃ አዉጭ ግንባር /ኦነግ/ ስራዊት ናቸዉ በተባሉና በኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት መካከል ላለፉት ቀናቶች ግጭት መታየቱን የአከባቢዉ የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬሌ ገልጹ። ግጭቱን ተከትሎ የክልሉ ፕሬስዳንት አቶ ለማ መገርሳ በትላንትናዉ እለት እንደተናገሩት ሁኔታዉ በጣም እንዳሳዘናቸዉ ገልፀዋል። ወጣቶች መሳርያ በመታጠቅ ዘመናዊ መሳርያ ከታጠቀዉ ከመንግስት ሰራዊት ጋር ለመወጋት ወደ ጫካ መግባታቸዉ ስህተት መሆኑን እና ትክክለኛ የትግል ስልት አለመሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ተችተዋል። አከባቢዉ ላይ ባለዉ የፀጥታ አለመረጋጋት ምክንያት የሰዎች እንቅስቃሴን እና የንግድ ሂደቱን ማገቱንም ገልፀዋል። ጫካ የገቡት እነዚህ ወጣቶች ወደ ቀያቸዉ እንዲመለሱ ለማድረግ ከሽማግሌዎች ጋር በመሆን እንደሚሞክሩ እንዲሁም ማህበረሰቡ በጠረጴዛ ዙርያ መወያያት እንደለበት አቶ ለማ አሳስበዋል። ይህ የማይሆን ከሆነ ለተከሰተዉና ለሚከሰተዉ ችግር መፍትሄ መስጠት እንደሚያስቸግር ገልፀዋል። ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች «መንግስት የኦነግ ስራዊት ለማጥቃት ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ» በመቃወም ወጣቶች ሰላማዊ ሰልፎችን እያደረጉ ይገኛሉ።
[5:03 PM, 10/29/2018] የዶይቸ ቬለ ዜና: የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮ ባደረጉላቸዉ ግብዣ ዛሬ ፓሪስ ፈረንሳይ የገቡት የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ረፋዱ ላይ ፓሪስ ቻርልስ ደጎል አዉሮፕላን ማረፍያ ሲደርሱ በርካታ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን አቀባበል አድርገዉላቸዋል። በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ዉስጥ የሚታየዉ የፀጥታ አለመረጋጋት የሚያሳስባቸዉ ግለሰቦች የጠቅላይ ሚንስትሩን የአዉሮጳ ጉብኝት አሁን መደረግ አልነበረበትም ሲሉ ትችታቸዉን ያቀርባሉ። እርሶስ ምን ይላሉ?
[7:48 PM, 10/29/2018] የዶይቸ ቬለ ዜና: ዋና ዋና ዜናዎቹ፤
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአውሮጳ ሃገራት ለሚያደርጉት ግብኝት ዛሬ ከቀትር በፊት ፓሪስ ገብተዋል። ከፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑዌል ማክሮ ጋር ስለሁለቱ ሃገራት ግንኙነት፤ ስለአካባቢ የፀጥታ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚካሄደው የማሻሻያ ለውጦች ፤ ንግድ እና መዋዕለ
የውሃ አቅርቦት ተስተጓጉሎ ለከተመባቸው የሐረር እና አካባቢው ከተሞች በቅርብ ቀናት ውስጥ የተለመደው የፈረቃ የውሃ አቅርቦት እንዲጀመር የጥገና ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸው ተገለጠ።
ከኢንዶኔዢያ ዋና ከተማ ጃካርታ አውሮፕላን ማረፊያ እንደተነሳ በተከሰከሰው የላየን ኤር አውሮፕላን 189 ተሳፋሪዎች ለሞት መዳረጋቸው የድርጅቱ የበረራ ቴክኒክ አቅምን ጥያቄ ላይ መጣሉ እየተገለጸ ነው። ዝርዝሩን ማገናኛውን በመጫን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤
https://www.wbca.st/ZgXIyLw